የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት ያሏቸውን የመሠረተ ልማቶችና በጋራ ተጠቃሚ በሚያደርጓቸው የአሰራር ስርዓቶች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ጥቅምት 14 ቀን 2017 . በኢትዮጵያ ፖስታ /ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራረሙ፡፡

በፊርማ ስነሥርዓቱ የኢኢግልድ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዢና ሽያጭ ዘርፍ /ዋና ሥራ አስፈጻሚ / አበባዬ ገዛኸኝ እንዲሁም በኢትዮጵያ ፖስታ የንግድ ዋና ስራ አስፈጻሚ / ትዕግስት በቀለ ድርጅቶቻቸውን በመወከል የመግባቢያ ሰነዱን ተፈራርመዋል፡፡

የኢትዩጵያ ፖስታ የረጅም ዓመታት ልምድና በመላ አገሪቱ 700 የሚጠጉ ቅርንጫፎች ያሉት የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 85 ዓመታት በላይ በንግዱ ዘርፍ የቆየና በመላ አገሪቱ 83 የሽያጭ ቅርንቻፎች ያሉት ድርጅት እንደሆነ በሁለቱም ድርጅቶች የበላይ አመራሮች ተነስቷል፡፡

ሁለቱም ድርጅቶች ያሏቸውን ይህንን እምቅ አቅም በመጠቀም ድርጅቶቻቸው የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ማማሳደግና ማሻሻል የሚቻልበትን አሰራር መዘርጋት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ስራ እንደተገባም የተገለጸ ሲሆን ይህም ድርጅቶቹ ያሏቸውን የመሠረተ ልማቶችና ያሏቸውን የአሰራር ስርዓቶች በመጋራት የድርጅቶቻቸውን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና የሀገርን ሐብት በአግባቡ ሥራ ላይ ማዋል ተገቢ እንደሆነ የድርጅቶቹ አመራሮች በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ አመላክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚያቀርብና ያመረቷቸውን ምርቶችም ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ፖስታ ደግሞ በአገራችን የፖስታ፣ የሎጀሰቲክስና ትራንስፖርት፣ የመንገድ ፈንድ ክፍያ፣ የብሔራዊ መታወቂያ እና የሰርተፍኬት ዕድሳት አገልግሎቶችን የሚሰጥ የመንግስት የልማት ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል፡፡