የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የበላይና መካከለኛ ሃላፊዎች በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓም በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ባዘጋጀው “ኑ ኢትዮጵያን እናልብሳት” አገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በችግኝ ተከላው መርሃግብር የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተካ ገብረየስ፣ ሌሎችም የበላይና መካከለኛ አመራሮችና የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሰራተኞች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በቀጣይም በተመሳሳይ መልኩ ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞቻቸውን በማስተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ የችግኝ መርሃ ግብር ማካሄድ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አሳስበዋል፡፡
በዕለቱ 2000 ችግኞች በኢንዱስትሪ ፓርኩ በተዘጋጀው ስፍራ ተተክለዋል፡፡
በመጨረሻም ችግኝ ተከላው እንደተጠናቀቀ ተሳታፊ ሚኒስትሮች፣ ሃላፊዎች እና ሠራተኞች በመቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት የጉብኝትና ምሳ ማብላት መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡
