ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ
ኢኢግልድ በስትራቴጂክ ዕቅዱና በአሰራር መመሪያዎች ረቂቅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቀቀ
13/05/2024
ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል
10/05/2024
ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ
09/05/2024
ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ
15/02/2024
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ
29/01/2024
የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ
17/01/2024
ማስታወቂያ
27/11/2023
የምግብ ዘይት በቫይታሚን ለማበልጸግ የሚያስፈልገውን የፕሪሚክስ አቅርቦትን አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ
06/11/2023
ኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ
06/11/2023
ማስታወቂያ
25/10/2023
ኢኢግልድ የ4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ
17/10/2023
ኢኢግልድ የ16.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ
14/09/2023
ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ
23/08/2023
የኢኢግልድ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በግንባታ ላይ የሚገኙና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮክቶችን ጎበኙ
31/07/2023
ኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካሄዱ
27/07/2023
የኢኢግልድ ሴት ሠራተኞች ፎረም ተመሰረተ
20/07/2023
ኢኢግልድ የ2015 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
11/04/2023
ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ
23/03/2023
ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ
18/01/2023
አርአያነት ያለው ተግባር
14/09/2022
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢግልድ) የዲስትሪክቶች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የተለያዩ ውስጣዊና ውጪያዊ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም ጥሩ ውጤትና የሚያበረታታ አፈጻጸም የተመዘገበበት መሆኑን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ ገለጹ፡፡
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይህንን የገለጹት የድርጅቱ የበጀት ዓመት አፈጻጸምና ዕቅድ እንዲሁም የዲስትሪክቶች የበጀት ዓመቱ አፈጻጸምና ዕቅድ ግምገማና ውይይት ከነሐሴ 13-14/2015 ዓ.ም በግዮን ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡
አያይዘውም የድርጅቱ አፈጻጸም አበረታች ቢሆንም በአፈጻጸም ወቅት የታዩ ክፍተቶች ተለይተው በቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የሚታረሙበት የአሰራር ሥርዓት ተዘርግተውላቸው አጥጋቢ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
በዚሁ መድረክ የማዕከላዊ፣ የምስራቅ፣ የምዕራብና የደቡብ ዲስትሪክቶች ሥር የሚገኙ የሽያጭ ቅርንጫፎች ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ በዲስትሪክቶቹ ሃላፊዎች እንዲሁም የድርጅቱ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ በስትራቴጂክ ሥራ አመራር ዳይሬክተር ቀርቦ ግምገማና ውይይት ተካሂዶ የጋራ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ተሰርቷል፡፡
በሁለቱ ቀናት ውይይት ዲስትሪክቶች ከዕቅድ እስከ አፈጻጸም ተናበው ለመስራት ያደረጓቸው ጥረቶችና የተገኙ ውጤቶች(የታዩ ክፍተቶች እንዳሉ ሆነው)አበረታች መሆናቸው፣ ሁሉም ዲስትሪክቶች ዕቅዶቻቸውን ከኮርፖሬት ዕቅዱ ጋር በመናበብ ለመፈጸም ያደረጉት ጥረት ሊበረታታ የሚገባው እንደሆነ፣ በሽያጭ ቅርንጫፎቻችን የሚገኙ የሸቀጦች ክምችት ጋር በተያያዘ ነባሩ አሠራር ትኩረት ሊሰጠውና ሊሻሻል እንደሚገባ፣ ለደንበኞች የተሠጠው ትኩረት ካለፉት ዓመታት የተሻለ ቢሆንም አሁንም ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበትና ሌሎችም ዓበይት ጉዳዮች ተነስተው የጋራ ግንዛቤ የተጨበጠባቸው ሲሆን ለግብዓት ግዢ የተገኘውን ብድር በጥቅም ላይ ማዋል፣ የድርጅቱ የሒሳብ ምርመራ፣ እየተገበሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶች እና የሪፎርም ሥራዎች ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑ ተብራርቷል፡፡
በሁለቱ ቀናት በአዳራሽ ከተካሄደው የውይይት በተጨማሪ የበላይ አመራሮች፣ የዲስትሪክት ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ባለ 18 ወለል የዋና መ/ቤት ሕንፃ ፕሮጀክት እንዲጎበኙና በፕሮጀክቱ የሚገኝበትን ደረጃ እንዲረዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ማብራሪያ በፕሮጀከቱ ሃላፊ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡