ኢኢግልድ በስትራቴጂክ ዕቅዱና በአሰራር መመሪያዎች ረቂቅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቀቀ

13/05/2024

ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል

10/05/2024

ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ

09/05/2024

ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ

15/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ

29/01/2024

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

17/01/2024

ማስታወቂያ

27/11/2023

የምግብ ዘይት በቫይታሚን ለማበልጸግ የሚያስፈልገውን የፕሪሚክስ አቅርቦትን አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ

06/11/2023

ኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ

06/11/2023

ማስታወቂያ

25/10/2023

ኢኢግልድ የ4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

17/10/2023

ኢኢግልድ የ16.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ

14/09/2023

ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ

23/08/2023

የኢኢግልድ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በግንባታ ላይ የሚገኙና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮክቶችን ጎበኙ

31/07/2023

ኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካሄዱ

27/07/2023

የኢኢግልድ ሴት ሠራተኞች ፎረም ተመሰረተ

20/07/2023

ኢኢግልድ የ2015 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

11/04/2023

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ

23/03/2023

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ

18/01/2023

አርአያነት ያለው ተግባር

14/09/2022

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 38 results.

ኢኢግልድ ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ውጤቶችን አቀረበ

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በ2013 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ከብር 2.7 ቢሊዮን በላይ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ውጤቶችን ለአምራች ኢንዱስትሪዎችና ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ፡፡


የድርጅቱ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እንደመለከተው ድርጅቱ ብር 322 ሚሊዮን የሚያወጡ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ለአምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም ብር 2.4 ቢሊዮን የሚያወጡ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ለተጠቃሚ የህብረተሰቡ ክፍሎች አሰራጭቷል፡፡


ኢኢግልድ ከኢንዱስትሪ ግብዓቶች ጋር በተያያዘ በጨርቃጨርቅና በአልባሳት፣ በቆዳ፣ በኢንዱስትሪ ጨው፣ በአግሮፕሮሰሲንግና በኮንስትራክሽን ግብዓቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሰርቷል፡፡ 


በዚህም መሠረት በጨርቃጨርቅ ከብር 14 ቢሊዮን በላይ፣ በቆዳ ዘርፍ ብር 526 ሺህ፣ በኢንዱስትሪ ጨው 22.44 ሚሊዮን፣ በአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ ብር 48 ሚሊዮን የሚያወጡ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ለማቅረብ ተችሏል፡፡


በተያያዘም ኢኢግልድ በመንግስት ከተሰጠው አምራች ኢንዱስትሪዎችን የመደገፍ ቁልፍ ስራ በተጨማሪ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያመርቷቸውን የኢንዱስትሪ ውጤቶች በመረከብ በተመጣጣኝ ዋጋ ያሰራጨ ሲሆን በያዝነው በጀት ዘመት ዘጠኝ ወራት ብር 2.4 ቢሊዮን የሚያወጡ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን አቅርቧል፡፡
በኢንዱስትሪ ውጤቶች ከተቀፉት ምርቶች መካከል ብር 1.4 ቢሊዮን የምግብ ዘይት፣ ብር 891 ሚሊዮን ስኳር፣ ብር 64 ሚሊዮን የሚያወጡ የጨርቃጨርቅ ምርቶች፤ከብር 14 ሚሊዮን በላይ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽንና ሌሎችም ምርቶች በማቅረብ በበጀት ዓመቱ የሚታየውን የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ንረትና የምርቶች አቅርቦት ችግሮችን ለማርገብ ትኩረት ተሠጥቶ ተሰርቷል፡፡


ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ በሙሉ አቅሙ የግዢ እቅዱን ለመፈጸም እንዳይችል የተለያዩ ተግዳሮቶች ያጋጠሙት እንደሆነ ሪፖርቱ ያመለከተ ሲሆን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር፣ ለግብዓቶች ግዢ ተደጋጋሚ ጨረታ ቢወጣም ተሳታፊ አለመኖር፣ የአቅራቢዎች የስምምነት ውል አለማክበር እና ከኢንዱስትሪ ጨው አቅራቢዎች ጋር ያለውን ችግር አለመፈታት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡