Responsive Image
  • የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ዘርፍ
    Responsibilities
    የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ዘርፍ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉትን አጠቃላይ የሥራ ድርሻና ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡
    Duties and Responsibilities
    • የዘርፉን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ ዕቅዶችን በማዘጋጀት በየሥራ ከፍሎቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል
    • የሚዘጋጀው ስትራቴጂክ ዕቅድ የገበያውን ሁኔታ ያገናዘበ እና የደንበኛውን ፍላጎት ማርካት የሚያስችል መሆኑን ያረጋግጣል፣
    • የገበያ ዳሰሳ ጥናቶችን በማከናወን ወቅታዊ የሆኑ የገበያ ፍላጎቶች መረጃዎችን ያሰባስባል፣ የተጠቃሚ እርካታዎችን በመዳሰስና ተንትኖ በማቅረብ በመረጃ መረብ አማካኝነት ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ እንዲደርስ ያደርጋል፣
    • የድርጅቱን የገበያ ወጪዎች በመተንተን የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ዋጋ ለመወሰን የሚያስችል ጥናት እንዲካሄድ ያደርጋል፤
    • በገበያው ላይ ብቁ ተወዳዳሪ በመሆን የገበያ ድርሻን ለማስፋት የገበያ ፍላጐትን የመለየትና የማጥናት ተግባራትን በበላይነት ይመራል፣ የማርኬቲንግ ስትራቴጂና ፖሊሲ ውጤታማነት ይገመግማል፣ የተለያዩ የማርኬቲንግ ዘዴዎችን በማጥናት ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ዘዴ በማፈላለግ አስተያየት ያቀርባል፡፡
    • የተወዳዳሪዎችን ሁኔታና ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎችን በየጊዜው በመዳሰስና በመረጃ መረብ አማካኝነት ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ እንዲደርስ ያደርጋል፣
    • ቀልጣፋና ውጤታማ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የአቅርቦት ሰንሰለት ማኔጅመንት መተግበር፤
    • የፕሮጀክት ጥናቶችን ሂደት ይከታተላል፤ በጥናቱ እንቅስቃሴ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ወቅታዊ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
    • በውጪና ሀገር በቀል ድርጅቶች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የፕሮጀክቶች ጥናት ሰነዶች ግምገማ ሥራዎች ላይ ይሳተፋል፤ በጥናቱ ዘርፍ ከውጭ አማካሪ ድርጅቶች ጋር በተጓዳኝነት መሳተፍ የሚችልበትን ሃሳብ ያቀርባል፤
    • ለኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት አቅርቦትና ሥርጭት ፕሮጀክቶች ጥናቶች የሚያስፈልገውን የባለሙያ ስብጥርና ብዛት በመወሰን የፕሮጀክት ጥናት ቡድኖችን ያደራጃል፣ የጥናት ሥራ መመሪያ ይሰጣል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
    • +251 11 369 22 43
  • የግዢ ዘርፍ
    Responsibilities
    የግዢ ዘርፍ ተጠሪነቱ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ያከናውናል፡፡
    Duties and Responsibilities
    • የድርጅቱን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዢን አስመልክቶ የረጅም፤ መካከለኛና የአጭር ጊዜ ስትራቴጂክ ዕቅድ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ ሲፀድቅም በየሥራ ከፍሎቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
    • የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ከአገር ውሥጥና ከውጭ አገር በመግዛት ማቅረብ፤
    • በአገር ውስጥና በውጭ አገር የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማምረት ማቅረብ፤
    • በአገር ውስጥና በውጭ አገር የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ግዢ በመፈጸም ለሚመለከታ ማቅረብ፤
    • በየበጀት ዓመቱ የሚከናወኑ ግዢዎችን በዓይነትና በመጠን በመለየት የግዢ እቅድ ያዘጋጃል፡ ሲፈቀድም ከሚመለከታቸው የሥራ ዘርፎች ጋር በመተባበር የግዢ ኘሮግራም ያወጣል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
    • ከፍተኛ ግዢዎች በጨረታ ወይም በቀጥታ ግዥ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር እንዲገዙ ሲወሰን አስፈላጊዎቹ ሰነዶችና የግዢ ፎርማሊቲዎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣ በደንብና መመሪያ መሠረት ግዢው እንዲፈጸም ያደርጋል፣
    • በጨረታ ለሚገዙ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የጨረታ ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ሲፈቀድም የጨረታውን አፈጻጸም ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
    • ተገዝተው ወደ ድርጅቱ መጋዘን የመጡ ዕቃዎችን ጥራትና የብዛት መጠን በማረጋገጥ ርክክብ መፈጸሙን፣ አስፈላጊ ምዝገባ መከናወኑንና በተገቢው መንገድ መከማቸቱን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፣
    • በዘርፉና በአፈፃፀሙ የላቀና ተወዳዳሪነትን የሚያመጣ ስልት መቀየስ፣ ተግባራዊ ማድረግ፣ ውጤቱን መገምገም፣
    • +251 11 369 24 41
  • የሽያጭ ዘርፍ
    Responsibilities
    የሽያጭ ዘርፍ ተጠሪነቱ ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ያከናውናል፡፡
    Duties and Responsibilities
    • የዘርፉን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ ዕቅዶችን በማዘጋጀት በየሥራ ከፍሎቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
    • የሽያጭና የክምችት መመሪያ በማዘጋጀት ሥራ ላይ ያውላል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
    • የድርጅቱን የግብአት ሽያጭ፣ ክምችትና ማከፋፈል ሥራዎች የሥራ ኘሮግራም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን በመገምገም ሪፖርት ያደርጋል፣
    • የአቅርቦትና የክምችት የሥራ ዘርፎችን ማደራጀት፣ ተግባራቸውን ማቀድ፣ ማስተባበር፣ መምራትና እያንዳንዱ ሥራ በተቀመጠለት የጊዜ ልኬት መሰረት መከናወኑን መቆጣጠርና አፈፃፀሙን መከታተል፣
    • የድርጅቱን የኢንዱስትሪ ግብዓቶች፤ የኢንዱስትሪ ውጤቶችና ሌሎች ንብረቶች ክምችት፣ አያያዝና ሽያጭ ሁኔታን ይከታተላል፣ የሚታዩ ችግሮችንና ጉድለቶችን በሚመለከት ተገቢው ዕርምጃ አንዲወሰድ ያደርጋል፣
    • የኢንዱስትሪ ውጤቶች ክምችት፣ ሥርጭትና ሽያጭ ሁኔታን ይከታተላል፣ የሚታዩ ችግሮችንና ጉድለቶችን በሚመለከት ተገቢው ዕርምጃ አንዲወሰድ ያደርጋል፣
    • የግብአትና የኢንዱስትሪ ውጤት ሽያጭ ገቢ በወቅቱ መሰብሰቡንና ገቢ መደረጉን ይከታተላል፡ ይቆጣጠራል፣
    • ወጪ የሚደረጉ የሽያጭ ዕቃዎች ኘሮሲጀሩ ተጠብቆ በተቀላጠፈ አሠራር በትክክል ለጠያቂው ክፍል መድረሳቸውን ያረጋግጣል፣
    • የዕቃ ማከማቻ መጋዘኖች የቦታ አጠቀቀም ሥርዓት ባለውና በሚገባ ለመጠቀም በሚያስችል ሁኔታ ያደራጃል፣ ለዕቃዎች በቂ ማከማቻ ሥፍራ መኖሩን ያረጋግጣል፣
    • በክምችት ሊያዙ የሚገባቸውን የሽያጭ ዕቃዎች ያቅዳል፣ ተገዝተው የሚመጡ ዕቃዎች በትክክል ገቢ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፣
    • በዓመታዊ የንብረት ቆጠራ ወቅት ንብረቶችን ያስቆጥራል በቆጠራ ወቅት ለሚነሱ ችግሮች ተገቢ መፍትሔ ይሰጣል፣
    • ተመርተው ወይም ተገዝተው ወደ መጋዘን የሚገቡ ምርቶችን ጥራትና የብዛት መጠን በማረጋገጥ ርክክብ መፈጸሙን፣ በትክክል ምዝገባ መከናወኑንና በተገቢው መንገድ መከማቸቱን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፣
    • ከዋና ሥራ አስፈጻሚ የሚሰጡትን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትንም ይፈጽማል፤ ያስፈጽማል፡፡
    • 011-369-22-94
  • የኮርፖሬት ሰርቪስ ዘርፍ
    Responsibilities
    የፋይናንስ፤ የሰው ሀብት፤ የግዢና የንብረት አስተዳደርና ሎጅስቲክስና ሕንጻ አስተዳደር ሥራዎች የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ ዕቅዶችን በማዘጋጀት በየሥራ ከፍሎቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
    Duties and Responsibilities
    • በድርጅቱ አጠቃላይ ደንብና መመሪያዎች መሠረት የድርጅቱን የዕድገት አቅጣጫ ጠቋሚ የሆነ የረዥም ጊዜ ስትራቴጂክ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፤
    • የድርጅቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተመለከተ ልዩ ልዩ ስታስቲካዊ መረጃዎቸን ያቀናብራል፤ ለሚመለከታቸው ያሠራጫል፤ የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፤ በየጊዜው የማሻሻያ ጥናት በመካሄድ የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል፤ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፤
    • የዕቃ ግዢ ጥያቄዎችን ይረከባል፤ የዋጋ መረጃ በመሰብሰብ ሂደት ይሳተፋል፤ ከአቅራቢዎች ዘንድ ያልተገኙ ዕቃዎችን ለጠያቂው ክፍል በወቅቱ ያሳውቃል፤ አማራጭ ዕቃዎችንና አቅራቢዎችን ዝርዝር ይመዘግባል፤
    • የድርጅቱ ንብረቶች በአግባቡ የሚያዙበትንና ለተፈለገው ዓላማ የሚውሉበትን ስልት ይቀይሳል፤ አገልግሎት አሰጣጥ ደንበኞችን በሚያረካ መልኩ መከናወኑን ይከታተላል፤ የንብረት አስተዳደር መመሪያዎችና ደንቦች በአግባቡ ሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤
    • የተሽከርካሪ አያያዝና ስምሪትን ያቅዳል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ተሽከርካሪዎችም በወቅቱ መጠገናቸውንና ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
    • በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች መሠረት ድርጅቱ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችል በጀት ያዘጋጃል፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
    • የሽያጭ ተሽከርካሪዎችን አያያዝና አጠቃቀም ለመቆጣጠር የሚያስችል የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱንና በቅንጅት መሥራታቸወን ያረጋግጣል፤
    • በድርጅቱ ደንብና መመሪያዎች መሠረት ለድርጅቱ ጥቅም የሚውሉ እቃዎችና አገልግሎቶ ግዥ በመፈጸም ለሚመለከታቸው ያቀርባል፣
    • የተሸከርካሪዎች ስምርት፤ የጥገና እና ሌሎች የጠቅላላ አገልግሎት ሥራዎችን ያከናውናል፤ በየጊዜው አፈጻጸማቸውን በመገምግም የመሻሻያ ሀሳብ ያቀርባል፤
    • የማስፈጸም አቅም ግንባታና የለውጥ ሥራ አመራር ተግባራት ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣ በተቋማት የለውጥ ኃይል እንዲበራከት ያደርጋል፣
    • በድርጅቱ የሚካሄዱትን የለውጥ ሥራዎች በአጠቃላይ ይመራል፣ ያስተባብራል፣ የአመራሩና የፈጻሚው አቅም እንዲገነባ ያደርጋል፣
    • የተቋማት ስራ አመራርና ሠራተኞች እንደየአስፈላጊነቱ የሚሰጡ ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን ያመቻቻል፤ ያስገኙትን ውጤት ይከታተላል ይገመግማል፤
    • ተቋማዊ ልማትን የሚያመጡ በምርጥ ተሞክሮ ላይ የተመሠረቱ አዳዲስ የአሰራር መሻሻያ ዘዴዎች በመቀመር ተፈጻሚ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤ ያስተባብራል፡፡
    • 011-369-22-94