የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ
10/11/2025
የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ
20/10/2025
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
10/10/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ
25/09/2025
የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
23/09/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
09/09/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ
27/08/2025
Financial and Audit Report 2021/22
12/05/2025
በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ
21/04/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ
17/03/2025
የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
17/03/2025
በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
11/03/2025
Financial and Audit Report 2020/21
28/01/2025
ማስታወቂያ
25/10/2023
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ
26/12/2024
የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ
02/12/2024
ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ
23/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
23/10/2024
በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ
14/10/2024
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
11/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች የድርጅቱን የ2017 በጀት ዓመት ስኬታማ አፈጻጸምና የታላቁን ህዳሴ ግድብ መጠናቅ ምክንያት በማድረግ ዛሬ ጷግሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በድምቀት አከበሩ፡፡
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክብርት ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ በስነስርዓቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እያከበርን ያለነው ይህ ክበረ በዓል በሁለት ምክንያቶች የተለየ እንደሆነ አመልክተው የመጀመሪያው የሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራ ያረፈበትና የኢትዮጵያዊያን ዳግማዊ የአድዋ ድል መገለጫ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቅ እና እንደተቋም በሁለተኛው የድርጅታችን ስትራቴጂክ እቅድ ማብቂያ ዓመት በሆነው 2017 በጀት ዓመት ዕቅዳችንን ካለፉት አራት ዓመታት በተሸለ ስኬት መፈጸማችን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ድርጅቱ በበጀት ዓመት የዕቅዱን 112 በመቶ አፈጻጸም ያስመዘገበ መሆኑን ያመለከቱት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ የተገኘው ውጤት የድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች ቅንጅትና ትብብር መሆኑን ገልጸው ይህም ቅንጅትና ተናቦ መስራት በ2018 በጀት ዓመትም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በተያያዘም የኢኢግልድ ስራ አመራር ቦርድ አባልና የሥራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢ ተወካይ አቶ ሸዋን ግዛው ማሞ ባደረጉት ንግግር እንዳመለከቱት በዓሉ የሚከበርበት በዛሬ ዕለት የህዳሴ ግድቡ የተጠናቀቀበት፣ ኢኢግልድ ካለፉት 4 ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ ውጤት የሰመዘገበበትና የአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ መሆኑ የድርጅቱንና የሀገራችንን የወደፊቱን መጪ ጊዜ ብሩህ መሆኑን የሚያበስር እንደሆነ ገልጻው እንኳን ለዚህ አበቃችሁ ብለዋል፡፡
አያይዘውም ይህ ውጤት የድርጅቱ ጠንካራ አመራሮች ባለሙያዎችና ሠራተኞች እንደሆነ አመልክተው ይህም የመኔጅመንቱና የሰራተኞች ቅንጅት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስተያታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም የድርጅቱ መሠረታዊ የሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ ግርማቸው ጫን ያለው ሰራተኞች በበጀት ዓመቱ ስላስመዘገቤት አመርቂ ውጤት፣ ስለማኔጅመንቴና የማህበሩ አመራሮች ተግባብቶ መስራት፣በቀጣይ የድርጅቱ ማኔጅመንትና የማህበሩ አመራሮች ትኩረት ሰጥተው በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ በማተኮር መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡፡



