የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ
10/11/2025
የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ
20/10/2025
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
10/10/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ
25/09/2025
የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
23/09/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
09/09/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ
27/08/2025
Financial and Audit Report 2021/22
12/05/2025
በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ
21/04/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ
17/03/2025
የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
17/03/2025
በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
11/03/2025
Financial and Audit Report 2020/21
28/01/2025
ማስታወቂያ
25/10/2023
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ
26/12/2024
የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ
02/12/2024
ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ
23/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
23/10/2024
በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ
14/10/2024
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
11/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የሽያጭ ቅርንጫፉ በቅርቡ ያቋቋመውና ስራ ያስጀመረው የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች መስከረም 9 እና 10/2018 ዓ.ም በአልሳም እና ቡሉኮ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት እና ምልከታ አካሄዱ፡፡
የፕሮጀክት ጥናት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ወ/ዮሐንስ እንደገለጹት ኢኢግልድ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የሽያጭ ቅርንጫፉ የክር ማጠንጠኛ ማዕከል አቋቁሞ የተጠነጠኑ ክሮችን ከፈትል እና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ገዝቶ ምርት በማምረት በማጠንጠን በሽመና ስራ ላይ ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች እና ኢንተርፕራይዞች ለገበያ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን የጉብኝቱ ዓላማም ማዕከሉ በቅርብ ቀን የተቋቋመ ከመሆኑ አንጻር በዘርፉ የካበተ ልምድ እና ተሞክሮ ካላቸው ተመሳሳይ ተቋማት ልምድ ወስደው የማምረት አቅማቸውን በማጎልበት በቀጣይ ማዕከሉን ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ ነው፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉት ሰራተኞች በሁለቱም ፋብሪካዎች የክር ማጠንጠኞ ክፍል በመገኘት ከምርት ግብዓት ዝግጅት ጀምሮ ምርት እስከሚመረትበት ደረጃ ፤ በእያንዳንዱ የምርት ሂደት የሚከናወኑ ተግባራቶችና የአመራረት ሂደቶች ፣ የምርት የጥራት አጠባበቅ ዘዴ፣ በምርት ጥራት አጠባበቅ ሂደት ላይ የሰራተኞቹ ሚና እና ድርሻ፤ የፋብሪካዎቹ የምርት የጥራት መለኪያ መስፈርቶች ፤ የፋብሪካ ሰራተኞች የሥራ ባህል እና ዲስፕሊን እንዲሁም በሌሎች ተጓዳኝ ጉዳዮች ላይ ሰራተኞቹ ግንዛቤ፤ ልምድ እና ተሞክሮ እንዱወስዱ ተደርጓል፡፡
በመስክ ጉብኝቱ የተሳተፉ ሰራተኞች እንደገለጹት ድርጅቱ ለማዕከሉ ሰራተኞች ትኩረት ሰጥቶ ይህን ጉብኝት ማዘጋጀቱ የስራ ተነሳሽነት የፈጠረላቸው ከመሆኑም በላይ ተጨማሪ ዕውቀት፣ ልምድ እና ግንዛቤ ያገኙበት እና ያገኙትንም ልምድ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸው እንደዚህ ዓይነት ፕሮግራሞች ቀጠይነት እንዲኖራቸው አስተያቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም በመስክ ጉብኝቱ የተገኙት ልምዶች እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ተቀምረው ወደ ማዕከሉ በማስፋት ተግባራዊ የሚሆንበት ሁኔታ እንደሚመቻች የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ወ/ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡



