በስድስት ወራት አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች ዕውቅና ተሰጠ
በስድስት ወራት አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች ዕውቅና ተሰጠ
27/01/2026
በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ
10/11/2025
የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ
20/10/2025
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
10/10/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ
25/09/2025
የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
23/09/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
09/09/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ
27/08/2025
Financial and Audit Report 2021/22
12/05/2025
በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ
21/04/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ
17/03/2025
የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
17/03/2025
በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
11/03/2025
Financial and Audit Report 2020/21
28/01/2025
ማስታወቂያ
25/10/2023
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ
26/12/2024
የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ
02/12/2024
ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ
23/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
23/10/2024
በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ
14/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለተገኘው ውጤት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የዲስትሪክቶችና የሽያጭ ቅርንጫፎች ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ዕውቅና ሰጠ፡፡
ኢኢግልድ ይህንን እውቅና የሰጠው የድርጅቱን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ለሁለት ቀናት እየገመገመ በሚገኝበት ወቅት ነው፡፡
አቶ ዳዊት አዳነ የኢኢግልድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ በዕውቅና አሰጣጥ ስነሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት ለተገኘው ውጤት የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የዲስትሪክትና የሽያጭ ቅርንጫፎች ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ባለፉት ስድስት ወራት የሳዩትን ተነሳሽነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ፤ በቀጣይም ሌሎቹ ቅርንጫፎች ዕውቅና ያገኙትን የስራ ክፍሎች እንደአርአያ በመውሰድ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባና ተሳትፏቸውንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በተካሄደው የግምገማና የውይይት መድረክ የድርጅቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የኦዲት ምርመራ ግኝት፤ የተመረጡ ቅርንጫፎች የግማሽ ዓመት አፈጻጸም፤ የአራቱ ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች አፈጻጸም እንዲሁም የኢኢግልድ የኮርፖሬት የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖቶች ቀርበው በጥልቀት ግምገማና ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ መደረክ ላይ እንደተነሳው በአፈጻጸም ወቅት የመፈጸም አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ቅርንጫፎች ምክንያቶች እንዲቀርቡና እንዲለዩ ተደርገው በስፋት ውይይት ተካሂዶባቸው የመፍትሔ ሐሳብ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡
በማጠቃለያም የድርጅቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ባለፉት ስድስት ወራት የተገኘውን የተሻለ ውጤት ለማስቀጠል ተግተው እንዲሰሩ ከድርጅቱ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አምራች ኢንደስትሪዎች ያለባቸውን የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍና የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያውን የማረጋጋት ሥራዎችን የሚያከናውን የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው።



