ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ
በስድስት ወራት አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች ዕውቅና ተሰጠ
27/01/2026
በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ
10/11/2025
የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ
20/10/2025
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
10/10/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ
25/09/2025
የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
23/09/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
09/09/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ
27/08/2025
Financial and Audit Report 2021/22
12/05/2025
በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ
21/04/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ
17/03/2025
የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
17/03/2025
በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
11/03/2025
Financial and Audit Report 2020/21
28/01/2025
ማስታወቂያ
25/10/2023
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ
26/12/2024
የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ
02/12/2024
ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ
23/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
23/10/2024
በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ
14/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ከጥር 30- የካቲት 5/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕብረት ሥራ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ባካሄደው 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ተሳተፈ ፡፡
በተዘጋጀው አገር አቀፍ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም በሃገሪቱ የተለያየ ክፍሎች የተደራጁ የሕብረት ሥራ ማሕበራት፣ የግብርና ምርት አቀነባበሪዎች፣ የኢንዱስትሪ/የፋብሪካ/ ባለቤቶች፣ የእርሻ መሣሪያ እና የግብርና ሜካናይዜሽን የሚያመርቱ/ከውጭ የሚያስመጡ/ ድርጅቶች፣ የግብርና ግብዓት አቅራቢ ድርጅቶች፣ የፋይናነንስ ተቋማት፣ የልማት አጋር ድርጅቶች፣ እንዲሁም ሌሎችም የአገልግሎትና የሥራ ግንኙነት ያላቸው ድርጅቶችና መ/ቤቶች ተሳትፈዋል፡፡
የዝግጅቱ ዓላማ ከሕብረት ስራ ማሕበራት ጋር ዘለቂ የገበያ ትስስር መፍጠር፣ የአምራቹንና ሸማቹን ህብረተሰብ የጋራ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ከኢንዱስትሪዎችና የምርት አቀናባሪዎች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ቀጣይነት ባለው መልክ ማስተሳሰርና የድርጅታችንን የኢንዱስትሪ ግብዓትና ውጤቶች አቅርቦት በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ አምራቾች የግብዓት ግዢና ሽያጭ ማሳለጥ ነው፡፡
በዚሁ ኤግዚቢሽንና ባዛር የሚሳተፉ ሃለፊዎችን ባለሙያዎች የኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦትን ለማከናወንና ሽያጩንም ለማሳለጥ በሚያስችሉ አሰራሮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፤ ሀገር አቀፍ ገዥዎች፣ አስመጪ እና ላኪዎች፣ የሴክተሩ የመንግስት ተወካዮች፣ የፋይናንስ ተቋማት እና የልማት አጋሮች እንዲሁም ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በመገናኘት በግብዓት ግዢና ሽያጭ የተሻለ የልምድ ልውውጥ የተካሔደ ሲሆን የንግድ ትስስር (Busines to Business Transaction) ለመመስረት የሚያስችሉ ግንኙነቶችን በማከናወን የጋራ መግባባት ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በ10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለያየ ዘርፍ በስራ ላይ የሚገኙ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

