EIIDE offered 16.5 million liters of edible oil at a reasonable price

14/09/2023

EIIDE conducted an evaluation of the of the 2022/23 fiscal year plan and the next year's plan of the enterprise

23/08/2023

Members of the Management Board visited projects of EIIDE

31/07/2023

Managers and Employees of EIIDE Conducted Green Legacy

27/07/2023

EIIDE has launched a women's workers forum

20/07/2023

ኢኢግልድ የ2015 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

11/04/2023

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ

23/03/2023

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ

18/01/2023

አርአያነት ያለው ተግባር

14/09/2022

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፍጆታ ምርቶች መሸጫ ዋጋ

09/09/2022

የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ በላቀ ሁኔታ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ

29/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ለአቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳት የማስጀመር እና የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናወኑ

07/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በ9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎቱን አስተዋወቀ

09/02/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ብር 265 ሚሊዮን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ተገለጸ

07/02/2022

በአዮዲን ያልበለጸገ ጥሬ ጨው ለምግብነት የሚያቀርቡ አካላት ከህገወጥ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ጥሪ ቀረበ

30/12/2021

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ለአቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳት የማስጀመር እና የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናወኑ

12/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ሰጠ::

02/09/2021

የኢኢግልድ አመራሮች በወረኢሉ ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አበረከቱ::

02/09/2021

ኢኢግልድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

02/09/2021

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግስት መርሃ ግብርን አካሄዱ

02/09/2021

— 20 Items per Page
Showing 41 - 60 of 67 results.

ድርጅቱ ተልዕኮውን በተሟላ ሁኔታ ለማሳካትና በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር የጀመራቸውን ጥረቶች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) የ2018 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ነው።

‎የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መና እንደገለጹት፣ የተቋሙ የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግልጽ፣ ተዓማኒ እና የአመራር ቅንጅት የታየበት ነው።ተቋሙ ቀደም ሲል በከባድ ችግር ውስጥ እንደነበር ጠቅሰው፣ የአመራር ለውጥ በማድረግ ከዚያ ሁኔታ መውጣቱንና አሁን በተሻለ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።ተቋሙ የኦዲት ግኝቶችን በየጊዜው ማረም፣ በዓለም የሚኖረውን ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በመቋቋም ሽያጭና ትርፍን ማስቀጠል፣ አዳዲስ ደንበኞችን ማምጣት እና የገበያ ተደራሽነትን በሚዲያ መሣሪያዎች ማሳደግ እንደ ጠንካራ አፈፃፀሞች ተጠቁመዋል።

‎እንዲሁም በግዥና ሽያጭ ሂደቶች ጥራትን ማረጋገጥ፣ የሴቶች የአመራር ተሳትፎን ማሳደግ እና የሰው ሀብት ልማት ሥርዓቱን ማጠናከር ተቋሙን ለሌሎች ድርጅቶች አርአያ የሚያደርገው መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ሥርዓት ለመተግበር የተደረጉ ዝግጅቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

‎‎ድርጅቱን በቀጣይ የሀብት አስተዳደርን ማሻሻል፣ የቅርንጫፍ ቢሮዎችን ማዘመን እና የዲጂታል ስርዓት ለማስፋት የተጀመሩ ሥራዎች እንዲጠናከሩ አሳስበዋል።‎የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ተቋሙ ከቋሚ ኮሚቴው ጋር ይበልጥ በመተባበር ለለውጥ የሚሠራ መሆኑን ገልፀው፣ ችግሮችን በጥናት፣ በዘላቂነትና በአስተማማኝ መልኩ ከሥር መሠረቱ ለመፍታት በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ያስጠናቸው ጥናቶች ጥሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። ይህንን ጥናት በማስተባበርና በማረጋገጥ ወደ ሥራ መግባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

‎በግዥ፣ በሽያጭና በተደራሽነት ዘርፎች የተቋሙ እቅዶችና አፈጻጸሞች የተሻሻሉ መሆናቸውን፣ ከኦዲት ጋር ተያይዞ የነበሩ ችግሮችም በተገቢ መንገድ መፍታታቸውን ገልፀው፤ ተቋሙን ለመለወጥ እና ሀብት ለማፍራት የሚደረጉ ጥረቶች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።‎ገበያውንና ወቅቱን በማየት የድርጅቱን ሕንጻ ዲዛይን በመቀየር ሙሉ በሙሉ ወደ ቢሮ አገልግሎት ለመለወጥ የተደረጉ ጥረቶች አበረታች መሆናቸውን እና ቀሪ የግንባታ ሥራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስረድተዋል።

በቀጣይ የድርጅቱን ይዞታ ማስከበር፣ የኢንዱስትሪ ጨው ግብዓት አቅርቦት አማራጮችን ማስፋት ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ብለዋል።‎የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ዳዊት አዳነ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ብቃት ባለው የሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ሥርዓት፣ ጠንካራ የአቅርቦትና የግብይት ሰንሰለት በመገንባት፣ ጥራታቸውን የጠበቁ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማልማትና በማቅረብ እንዲሁም የተመረጡ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ለተጠቃሚዎች በማድረስ፣ የሀገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ውጤታማነት እንዲጨምር እና የገበያ መረጋጋት እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

‎‎ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 9 ወራት እቅድ አፈፃፀሙ በኢንዱስትሪ ግብዓቶች እና ውጤቶች ግዥ እና ሽያጭ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ጠቁመው፣ ተቋሙ በበጀት አመቱ 580 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ለቋሚ ኮሚቴው ተናግረዋል።‎በበጀት ዓመቱ ለኢንዱስትሪ ጨው አቅርቦት አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆን ምክንያት የነበሩ ጉዳዮችን በቀጣይ በመፍታት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ጥረት የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡